መግቢያ
እንኳን ወደ አሃዱ መመሪያ በሰላም መጡ።
አሃዱ ለ ኢትዮጲያውያን የተዘጋጀ ፕሮግራም የመጻፊያ ቋንቋ ነው።
አሃዱ የተለያዩ ኢትዮጵያዊ የሆኑ ቃላቶችን በመጠቀም ፕሮግራም መጻፍ ያስችላል። ይህም እኛ ኢትዮጲያውያን የተለያዩ አቅም ያላቸው ፕሮግራሞችን በራሳችን ቋንቋ መጻፍ ያስችለናል።
በግራ በኩል የመመሪያውን መንቀሳቀሻ ያገኙታል። እሱም ተራ በተራ መመሪያውን ለመከታተል ያስችልዎታል። ቢሆንም ግን ማንበብ ፈልገው የመጡት ግልጽ ነገር ካለ ወደዛ ገጽ በመሄድ ማንበብ ይችላሉ።
ለመጀመር አሃዱን መጫንን ይመልከቱ።
Info
ይህ መመሪያ ለጀማሪ የተሰራ ቢሆንም እንዴት ፕሮግራም እንደሚደረግ ግን አያስተምርም። እሱን በሌላ የፕሮግራም ቋንቋዎች ቀድመው ማወቅ ይኖርብዎታል።