ክፍሎች
ክፍሎች ነገር ተኮር ፕሮግራሞችን መስሪያ መንገዶች ናቸው።
ክፍሎችን እንደሚከተለው እንሰይማለን
ክፍል የዋጋ_አወጣጥ {
// class body
}የክፍል ማስጀመሪያ መንገድ ለየት ያለ ተግባር ሲሆን ነገሮችን እንደማስጀመሪያነት እንጠቀምበታለን። በአንድ ክፍል ውስጥ አንድ ማስጀመሪያ ብቻ ነው መሰየም የሚቻለው።
ክፍል የዋጋ_አወጣጥ {
ማስጀመሪያ(ብር, ምንዛሪ) {}
// class body
}አሁን ላይ ያለውን ነገር ወይም ክፍል ለመጥቀስ ወይም ለመጥራት ይህ የትባለውን ቁልፍ ቃል እንጠቀማለን።
ክፍል የዋጋ_አወጣጥ {
ማስጀመሪያ(ብር, ምንዛሪ) {
ይህ.ብር = ብር;
ይህ.ምንዛሪ = ምንዛሪ;
}
// class body
}ከላይ አሁን ላይ ያለውን ነገር ብር እና ምንዛሪ እየሰየምኩ ነው።
የክፍል መንገድን ለመሰየም ማስጀመሪያን የሰየምንበትን መንገድ እንጠቀማለን።
ክፍል የዋጋ_አወጣጥ {
ማስጀመሪያ(ብር, ምንዛሪ) {
ይህ.ብር = ብር;
ይህ.ምንዛሪ = ምንዛሪ;
}
ዋጋውን_አውጣ() {
አውጣ ይህ.ብር + " " + ይህ.ምንዛሪ;
}
}
መለያ ዋጋ = የዋጋ_አወጣጥ(100, "Dollar");
ዋጋ.ዋጋውን_አውጣ(); // prints 100 Dollarአንድ ክፍል አንድ ክፍልን ይወርሳል ለማለት አዲስ በሚፈጠረው ክፍል (በወራሹ ክፍል) እና አዲሱ ክፍል የሚወርሰው ክፍል መሃል < ቁለፍ ቃልን እንጠቀማለን።
አንድ ክፍል አንድ ክፍልን ወረሰ ስንል ወራሹ ክፍል የተወራሹን ሙሉ ባህርይ ይወስዳል ማለታችን ነው።
ክፍል ምንዛሪ {
ማስጀመሪያ(የምንዛሪ_አይነት) {
ይህ.የምንዛሪ_አይነት = የምንዛሪ_አይነት;
ከሆነ (የምንዛሪ_አይነት == "Dollar") {
ይህ.ኮድ = "$"
} ካልሆነ {
ይህ.ኮድ = የምንዛሪ_አይነት
}
}
}
ክፍል የዋጋ_አወጣጥ < ምንዛሪ {
ማስጀመሪያ(ብር, ምንዛሪ) {
ታላቅ(ምንዛሪ);
ይህ.ብር = ብር;
}
ዋጋውን_አውጣ() {
አውጣ ይህ.ብር + " " + ይህ.የምንዛሪ_አይነት + " (" + ይህ.ኮድ + ")";
}
}
መለያ ዋጋ = የዋጋ_አወጣጥ(100, "Dollar");
ዋጋ.ዋጋውን_አውጣ(); // prints 100 Dollar ($)ታላቅ ምንድነው ብለው የጠይቁ የሆናል ታላቅ ተወራሹን ክፍል የምንጠራበት መንገዳችን ነው እናም ከላይ ታላቁን ክፍል ማስጀመሪያው ከሚፍለጋቸው መለኪያዎች ጋ እያስጀመርኩት ነው። ታላቅን ሌላ የ ፕሮግራም ቋንቋዎች ላይ super በማለት እናውቀዋለን።