መለያ
መለያዎች ነገሮችን ማስቀመጫ ቦታ ናቸው።
መለያዎች ነገሮችን በመለያው ስም በማቀመጥ ነገሮቹን በመለያው ስም መልሶ ማግኘት ያስችሉናል።
ነገሮችን በስማቸው ከመጥራታችን በፊት ልናውጃቸው ይገባል። መለያዎችን ደግሞ መለያ የተባለ ቁልፍ ቃልን በመጠቀም እናውጃለን
መለያ ስም;ስም የመለያው ስም ነው። ስም ሁሉም አይነት የላቲን ፊደሎች እና አማረኛ ፊደሎች መሆን ይችላሉ። በቁጥር እስካልጀመሩ ድረስ እና የተያዙ ቃላቶች እስካልሆኑ ድረስ የአጻጻፍ ሁኔታዎች ላይ እንደተገለጸው።
ሁሉም መለያ በቀጥታ የሆነ ነገር እስካልሰጠነው ድረስ ያ ስም የያዘው ነገር ባዶ ይሆናል። ባዶ በ አሃዱ በዛ መለያ ውስጥ ምንም እንደሌለ ያመላክታል።
መለያ ስም;
መለያ ሌላ_ስም = ባዶ; እዚህ ጋ ባዶን ሌላ_ስም ስም ብዬ እየሰየምኩ ነው። አሁን ላይ ሁለቱም ስምም ሆነ ሌላ_ስም ባዶ ናቸው።
መለያ ስም = 10;
አውጣ ስም; // 10 ብሎ ያወጣል።በ አሃዱ ውስጥ ሁለት አይነት መለያዎች አሉ: ውስጣዊ መለያዎች እና ውጪያዊ መለያዎች
ውስጣዊ መለያዎች በ አጥር እይታ ውስጥ የተሰየሙ መለያዎች ሲሆኑ ውስጣዊ መለያዎችን ማግኘት የሚቻለው በዛው በተሰየሙበት አጥር ውስጥ ብቻ ነው።
ውጪያዊ መለያዎች ከማንኛውም አጥር ውጪ የተሰየሙ መለያዎች ሲሆኑ ውጪያዊ መለያዎችን ከ የትኛውም እይታ ውስጥ ማግኘት ይቻላል።