ተግባሮች
ተግባር አንድ ተግባርን ለመፈጸም ተቀናጅቶ የተቀመጠ ኮድ ነው።
ተግባርን እንደሚቀጥለው ተግባር የተባለ ቁልፍ ቃልን በመጠቀም መሰየም ይቻላል:
ተግባር ደምር(ቁጥር1, ቁጥር2) {
// የተግባር አካል
}ደምር የተግባሩ መለያ ስም ሲሆን ቁጥር1 አና ቁጥር2 ይህ ተግባር የሚጠብቃቸው መለኪያዎች ናቸው። አንድ ተግባር 0 እና ከዛ በላይ መለኪያዎችን ሊቀበል ይችላል።
አንድ ተግባር መልስ እንዲሰጥ እስካልተደረገ ድረስ ባዶ ነው የሚመልሰው። መልስ መስጠት ሲፈለግ እንደሚከተለው መልስ ቁልፍ ቃልን በመጠቀም መልስ መስጠት ይቻላል።
ተግባር ደምር(ቁጥር1, ቁጥር2) {
መልስ ቁጥር1 + ቁጥር2;
}ይህ ተግባር እንደመለኪያ የተቅበላቸውን ሁለት ቁጥሮች ድምር መልስ ይሰጣል።
ተግባሮችን መጥራት እስካልቻልን ድረስ ጥቅም የለሽ ሆነው የቀመጣሉ ስለዚህ የምንጠራበት መንገድ ያስፈልገናል። ተግባሮችን እንደሚከተለው መጥራት እንችላለን
ተግባር ደምር(ቁጥር1, ቁጥር2) {
መልስ ቁጥር1 + ቁጥር2;
}
መለያ ውጤት = ደምር(1, 2);
አውጣ ውጤት; // 3 ብሎ ያወጣልከላይ ደምር ተግባርን 1 እና 2 ን እንደ መለኪያ አድርጌ ጠርቼ ያገኘሁትን መልስ ደግሞ ውጤት መለያ ውስጥ እያስቀመጥኩ ነው።
Warning
ደምር 2 መለኪያዎችን ይጠብቃል 1 ወይም 0 መለኪያዎችን አሳልፌ ቢሆን ኑሮ ስህተት ይፈጠር ነበር። ስለዚህ ሁሌም ተግባሩ የሚብቃቸውን መለኪያዎች መርሳት የለብንም።
ተግባር ደምር(ቁጥር1, ቁጥር2) {
መልስ ቁጥር1 + ቁጥር2;
}
መለያ ውጤት = ደምር(1); // error