እስከ ተመላላሽ

እስከ ተመላላሽ አጥር ውስጥ ያሉትን የኮድ ገለጻዎች የተገለጸው ሁኔታ እውነት እስከሆነ ድረስ ለመተግበር ይረዳል

እስከ (ሁኔታ) {
    // የ ኮድ ገለጻዎች
}

የእስከ ሁኔታ ከለዚህ ሁኔታ ጋር ተመሳሳይ ሲሆን የተመላላሹን ማስቆሚያ ቅድመ ሁኔታ ለማስቀመጥ ይረዳናል። ይህም ማለት ተመላላሹ ቅድመ ሁኔታው እውነት እስከሆነ ድረስ ብቻ ነው የሚመላለሰው።

የሚከተለው የለዚህ ተመላላሽ ሀ ከ10 እስካነሰ ድረስ በመመላለስ በ እያንዳንዱ ምልልሶሽ ደግሞ አሁን ላይ ሀ ያለውን እሴት ያወጣል።

ልብ ይበሉ ሀን በእያንዳንዱ ምልልሶሽ በ1 እያሳደግኩ ነው። ያንን ያላደረግኩ እንደሆን ማለቂያ የሌለው ተመላላሽ ይፈጠራል።

መለያ = 0;
 
እስከ (ሀ < 10) {
    አውጣ ሀ;
 = ሀ + 1;
}