ማጣመር እና ማጠር
የ ኮድ ገለጻዎችን ማጣመር እና ማጠር
አጥር ውስጥ ያሉ የ ኮድ ገለጻዎች በቅደም ተከተል የሚተገበሩ ዝርዝር የ ኮድ ገለጻዎች ናቸው። የኮድ ገለጻዎችን በ {} ቁልፍ ቃል ማጠር ይቻላል።
በ አጥር ውስጥ የተሰየሙ ማንኛውንም ስያሜዎችን ከ አጥሩ እይታ ውጪ ማግኘት አይቻልም። ይህም ማለት
መለያ ውጪያዊ_መለያ = 5;
{
መለያ ውስጣዊ_መለያ = ውጪያዊ_መለያ + 10; // ውጪያዊ መለያን ከ ውስጥ ሆኜ ማግኘት እችላለሁ ውጤቱም 15 ይሆናል
}
ውጪያዊ_መለያ = ውስጣዊ_መለያ; // ነገር ግን ውስጣዊ መለያን ከ ውጪ ሆኜ ማግኘት አልችልም ውስጣዊ መለያ ከ እይታ ውጪ ነውውስጣዊ መለያን ማግኘት የምችለው በተመሳሳይ እይታ ወይም ከሱ በታች ካለ እይታ ውስጥ ሆኜ ብቻ ነው
{
መለያ ውስጣዊ_መለያ = 5;
{
ውስጣዊ_መለያ = ውስጣዊ_መለያ + 1; // 6
{
ውስጣዊ_መለያ = ውስጣዊ_መለያ + 1; // 7
}
}
}የማጣመር ኦፕሬተር () የ ኮድ ገለጻዎችን በማጣመር ቅድሚያ አሰጣጥ ሁኔታውን ለመቆጣጠር ያገለግላል
ይህንን ምሳሌ የመልከቱ
መለያ ሀ = 1;
መለያ ለ = 2;
መለያ ሐ = 3;
// ነባር ቅድሚያ አሰጣጥ
አውጣ ሀ + ለ * ሐ; // 7 ብሎ ያወጣል
// በነባር እንደዚህ ያየዋል
አውጣ ሀ + (ለ * ሐ); // 7 ብሎ ያወጣል
// አሁን ቅድመ አሰጣጡን በመቆጣጠር
// ከ ማባዛት በፊት መደመር
አውጣ (ሀ + ለ) * ሐ; // 9 ብሎ ያወጣል