ለዚህ ተመላላሽ
ለዚህ ተመላላሽ በ አጥር ውስጥ ያሉ የ ኮድ ገለጻዎችን ለተወሰነ ጊዜ ለመደጋገም ይጠቅማል
ለዚህ ተመላላሽ በ አጥር ውስጥ ያሉትን የ ኮድ ገለጻዎችን ቅድመ ሁኔታው እውነት እስከሆነ ድረስ በተደጋጋሚ ይፈጽማል።
ለዚህ (መለያ = የኮድ_ገለጻ; ሁኔታ; መጨመር) {
// የኮድ ገለጻዎች
}በ መለያው ክፍል አዲስ መለያ መሰየም ይቻላል
ለዚህ (መለያ ሀ = 0; ሁኔታ; መጨመር) {
// የኮድ ገለጻዎች
}ወይም ደግሞ የተሰየመ መለያ መጠቀምም ይቻላል
መለያ ሀ;
ለዚህ (ሀ = 0; ሁኔታ; መጨመር) {
// የኮድ ገለጻዎች
}ወይም ደግሞ ባዶውንም መተው ይቻላል ነገር ግን ሴሚኮሎኑን ማስገባት አለብን። የ መለያ ስየማው ማብቃቱን ለመጠቆም
ለዚህ (; ሁኔታ; መጨመር) {
// የኮድ ገለጻዎች
}የለዚህ ሁኔታ የተመላላሹን ማስቆሚያ ቅድመ ሁኔታ ለማስቀመጥ ይረዳናል። ይህም ማለት ተመላላሹ ቅድመ ሁኔታው እውነት እስከሆነ ድረስ ብቻ ነው የሚመላለሰው።
Warning
ሁኔታውን ባዶውን መተው ማለቂያ የሌለው ተመላላሽ ስለሚያስከትል ማለቂያ የሌለው ተመላላሽ ሲፈልጉ ብቻ ይተዉት።
ለዚህ (መለያ ሀ = 0; ሀ < 10; መጨመር) {
// የኮድ ገለጻዎች
}ይህ ኮድ ሀ ከ 10 በታች እስከሆነ ድረስ ብቻ ነው የሚመላለሰው።
Info
ለምን ያህል ጊዜ ተመላላሹ መመላለስ እንዳለበት አስቀድሞ የማይታወቅ ከሆነ እስከ ተመላላሽን ቢጠቀሙ ይመከራል።
የለዚህ መጨመር ክፍል ከያንዳንዱ ምልልሶሽ በሗላ የሚተገበር ክፍል ሲሆን ይህም የት በ ተመላላሹ ውስጥ የት እንዳለን ለማወቅ የተተቀምነውን እሴት ለማሳደግ ይረዳናል።
ለዚህ (መለያ ሀ = 0; ሀ < 10; ሀ = ሀ + 1) {
// የኮድ ገለጻዎች
}ይህ ኮድ በእያንዳንዱ ምልልሶሽ ሀን ያሳድጋል ይህም ምልልሶሹ 10 ጊዜ ብቻ እንዲከናወን ያደርገዋል ማለት ነው።