መግቢያ
ይህ ምእራፍ የ አሃዱን አጻጻፍ ያሳያል
አሃዱ ያ አብዛኞቻችን የምናውቀውን የC ን አይነት የአጻጻፍ ስልት ይከተላል። ስለዚህ ቶሎ ለመረዳት ቀላል ይሆንልዎታል። በዛ ላይ ደግሞ ነጻ የሆነ ቋንቋ ነው በ ቃላቶች መካከል የሚከሰቱ ባዶ ቦታዎችን ይዘላል።
የ አሃዱ ስሞች ሁሉም አይነት የላቲን ፊደሎች እና አማረኛ ፊደሎች መሆን ይችላሉ። በቁጥር እስካልጀመሩ ድረስ እና የተያዙ ቃላቶች እስካልሆኑ ድረስ። የ አሃዱ ስሞች መለያዎችን, ክፍሎችን እና ተግባሮችን ለመሰየም ያገለግሉናል።
| እውነት | ሀሰት | እና | ከሆነ |
| ካልሆነ | እስከ | ለዚህ | መለያ |
| ተግባር | ክፍል | ይህ | ባዶ |
| ታላቅ | መልስ | አውጣ | ወይም |