ኦፕሬተሮች

  • +: መደመር
  • -: መቅነስ
  • *: ማባዛት
  • /: ማካፈል
  • %: የማካፈል ድርሻ
  • -: አሉታ ቀያሪ
  • ==: እኩልነት
  • <: ያንሳል
  • >: ይበልጣል
  • <=: ያንሳል ወይም እኩል ይሆናል
  • >=: ይበልጣል ወይም እኩል ይሆናል
  • !=: እኩል አይደሉም

አፍራሽ ኦፕሬተር ! ሁል ጊዜም እውነት ወይም ሀሰት ብሎ ይመልሳል። የግንኙነት ኦፕሬተር እና የመጀመሪያውን መለኪያ ሀሰት ወይም ባዶ ከሆነ የመጀመሪያውን መለኪያ ይመልሳል። ካልሆነ እና ሁለተኛውን መለኪያ ይመልሳል። የመለያ ኦፕሬተር ወይም የመጀመሪያው መለኪያ ባዶ ወይም ሀሰት ካልሆነ የመጀመሪያው መለኪያ ይመልሳል። ካልሆነ ወይም ሁለተኛውን መለኪያ ይመልሳል። ሁለቱም እና እና ወይም የ አጭር ጊዜ ግምገማን ይጠቀማሉ። ይህም ማለት ሁልተኛው መለኪያ አስፈላጊ ከሆነ ብቻ ነው የሚታየው ማለት ነው።

  • ወይም
አውጣ 10 ወይም 20; // 10
አውጣ 10 ወይም ባዶ; // 10
አውጣ ባዶ ወይም 10; // 10
  • እና
አውጣ 10 እና 20; // 20
አውጣ 10 እና ሀሰት; // ሀሰት
አውጣ ሀሰት እና 10; // ሀሰት
  • !
አውጣ !ሀሰት; // እውነት
አውጣ !እውነት; // ሀሰት