ሁኔታዊ ገለጻዎች

ሁኔታዊ ገለጻዎች የገለጻውን አካሄድ እንደ ሁኔታው ለመቀየር ይረዱናል።

ከሆነ ካልሆነ ገለጻዎች በሁኔታዎች ላይ ተመርኩዞ ድርጊቶችን ለመፈጸም ይረዱናል።

  • ከሆነን ሁኔታው እውነት ከሆነ አጥር ውስጥ ያለውን የኮድ ገለጻ ለመፈጸም እንጠቅምበታለን።
  • ካልሆነን ሁኔታው ሀሰት ከሆነ አጥር ውስጥ ያለውን የኮድ ገለጻ ለመፈጸም እንጠቅምበታለን።
ከሆነ (ሁኔታ) {
    // ሁኔታው እውነት ከሆነ የሚፈጸም ኮድ
}

ሁኔታ ውጤቱ እውነት ወይም ሀሰት የሆነ የኮድ ገለጻ። የትኛውም አውንታዊ ቁጥር እውነት ሲሆን እና የትኛውም አሉታዊ ቁጥር ሀሰት ነው። በተጨማሪም ባዶ እና ሀሰት ሀሰት የሆነ ውጤት ያመጣሉ ይህም ማለት በ አጥር ውስጥ ያለው ኮድ አይፈጸምም ማለት ነው።

ከሆነ (እውነት) {
    አውጣ "ይህ ይፈጸማል።";
}
 
ከሆነ (ሀሰት) {
    አውጣ "የህ አይፈጸምም።";
}

ካልሆነን የከሆነ ሁኔታ ሀሰት ሲሆን እንዲፈጸም የምንፈልገውን የ ኮድ ገለጻ ለመግለጽ እንጠቅምበታለን።

ከሆነ (ሀሰት) {
    አውጣ "ይህ አይፈጸምም።";
} ካልሆነ {
    አውጣ "ይህ ይፈጸማል።";
}
 
ከሆነ (እውነት) {
    አውጣ "ይህ ይፈጸማል።";
} ካልሆነ {
    አውጣ "ይህ አይፈጸምም።";
}